Pakistan Embassy at Ethiopia Adis Ababa, Pakistan Flag
Pakistan Embassy Ethiopia Adis Ababa, Ethiopia Flag

News

img

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ : የኤግዚህቢሺን ኩነት አዘጋጅ ድርጅቶችን አወዳድሮ መቅጠር >>ተጨማሪ ያንብቡ >>

September 23rd, 2024

በአዲስ አበባ የሚገኘዉ የፓኪስታን እስላማዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ የንግድ ክፍል በሚሊኒየም አዳራሽ, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ ከጥር 15-17፣ 2025 (እ.ኤ.አ.) የሚካደዉን 5ኛውን የፓኪስታን-አፍሪካ የንግድ የልማት ኮንፈረንስ (PATDC) እና የነጠላ ሀገር ኤግዚቢሽን (SCE) ለማደራጀት በኢትዮጵያ ህጋዊ ሆነዉ የተመዘገበ አንድ የኩነት (ኢቨንት ማኔጅመንት) አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ በጨረታ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ No. TDAP/IMDD/5thPATDC/Ethiopia/2024 የኤግዚህቢሺን ኩነት አዘጋጅ ድርጅቶችን አወዳድሮ መቅጠር በአዲስ አበባ የሚገኘዉ የፓኪስታን እስላማዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ የንግድ ክፍል በሚሊኒየም አዳራሽ, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ ከጥር 15-17፣ 2025 (እ.ኤ.አ.) የሚካደዉን 5ኛውን የፓኪስታን-አፍሪካ የንግድ የልማት ኮንፈረንስ (PATDC) እና የነጠላ ሀገር ኤግዚቢሽን (SCE) ለማደራጀት በኢትዮጵያ ህጋዊ ሆነዉ የተመዘገበ አንድ የኩነት (ኢቨንት ማኔጅመንት) አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ በጨረታ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል። 2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተዛማጅ መረጃዎችን ከፓኪስታን እስላማዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ የንግድ ክፍል በጽሁፍ ሲጠይቁ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ወይም ከዚህ በታች ያለውን የድህረ-ገጽ ማስፈንጠሪያ አድራሻ በመጠቀም ከፓኪስታን እስላማዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ ፣ ከፓኪስታን ንግድና ልማት ባለስልጣን እና ከፓኪስታን የመንግስት ግዥ ቁጥጥር ባለስልጣን (PPRA) ድህረ-ገጽ ማዉረድ ይችላሉ። 3. የነጠላ ደረጃ ሁለት ኤንቨሎፕ ሂደት፣ በ PPRA ሕጎች 36 (ለ) የ PPRA ሕጎች መሠረት፣ ክፍት ጨረታዉ ጥቅም ላይ ይውላል። ተጫራቾች በተለያዩ ኪስ-ወረቀቶች የታሸገ የቴክኒክ ፕሮፖዛል እና የፋይናንሺያል ፕሮፖዛል በደማቅ እና በሚነበብ መልኩ በተፃፈ ደብዳቤ ግራ በማያጋባ ሁኔታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡ሁለቱ ፐሮፖዛሎች በአንድ ትልቅ ከረጢጥ ዉስጥ ተደርጎ የተጫራቹ መ/ቤት ስም መፃፍ አለበት፡፡የፋይናንሺያል ፕሮፖዛል ከጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ (2%) የጨረታው መጠን በክፍያ ማዘዣ/በባንክ ረቂቅ/የባንክ ዋስትና በዶላር ወይም ተመጣጣኝ በሆነ የዶላር ምንዛሪ መጠን ብር ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት ተያይዞ በታሸገ የፋይናንሻል ፕሮፖዛል ጋር አብሮ መቅረብ ይኖርበታል። 4. የታሸጉ የጨረታ ሰነዶች እስከ ሰኞ, መስከረም 27 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጥር ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ የሚገኘዉ የፓኪስታን እስላማዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ የንግድ ክፍል በአካል መቅረብ አለባቸው። የቴክኒክ ፕሮፖዛሉ በዚሁ ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጥር ከቀኑ 9፡30 የተሳታፊዎች ተወካዮች እና የጨረታ ኮሚቴው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።የቴክኒክ ፕሮፖዛላቸዉ ብቁ የሆኑ ኩባንያዎች የፋይናንስ ፕሮፖዛል ብቻ በጨረታ ኮሚቴው በተገለጸው ቀን ይከፈታል፡፡ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱትን ሁሉንም መስፈርቶች የማሟሉ ተጫራቾች ብቻ ተቀባይነት ያገኛሉ. የመጨረሻዉ ግምገማ በ PPRA ድህረ ገጽ (በ PPRA ሕጎች መሠረት) የቻረታዉ ዉጤት ከመገለጹ በፊት ይደረጋል፡፡ 5. TDAP፣ የንግድ ክፍል፣ የፓኪስታን እስላማዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ እና የጨረታ ኮሚቴ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ነገር ግን ውድቅ የተደረገበት ምክንያት ወይም የጨረታውን ማፍረስ ሂደት በግዥ ደንቡ መሰረት ለሚመለከተው ተጫራች ይገለጻል። Website: https://et.pakembassy.org/ http://tdap.gov.pk http://ppra.org.pk The Commercial Section, Embassy of Islamic Republic of Pakistan Arada 13/14, Addis Ababa, Ethiopia Email: mti.addisababa@commerce.gov.pk Contact: +251-111-261-492 | +251-111-261-193